‘የሰላም ድምፆች’ (Voices for Peace) የግጥም ስብስብ – ሕትመት ጥሪ

No comments

 

የጻሃፍያን ማህበር – ፐን ኤርትራ በስደት፥  የኢትዮጵያንና የኤርትራ ሀገር ገጣሚያንን ድምፆች በአንድ የስነ-ጽሁፍ ቦታ በማገናኘት የስነ-ግጥም ስብስብ ለማሳተም አስቧል፤ የዚህም ህትመት አካል ይሆኑ ዘንድ የሁለቱም ሀገራት ገጣሚያንን ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።

ስለ ስብስቡ

ስነ-ጥበብ በአብዛሃኛው ተገቢውን ትኩረት በማያኘበትና ለጠባብ አጀንዳዎች በሚውልበት ወቀት ይህ ‘’የሰላም ድምፆች’’ ህትመት ጥሪ በአንፃሩ ጥበባትን እንደ ብረቱ ምስክርነት ይመለከታቸዋል።

ይህ ስብስብ ሰላምን እንደ መዳረሻ አድማስ በመያዝ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎችና የሚሰበስባቸውን ድምፆች በአንድ ይቀርጻል ።

ይህ ስብስብ ከመነሻው የመፍትሄ ሀሳቦችን የማቅረብ ወይም ትርክቶችን የመጫን አላማ የለውም፤ ይልቁንም ገጣሚያኑ በትውስታ፣ በግጭት፣ በስደት፣ በመትረፍ፣ በቅርርብ፣ በዝምታ ወይም በተስፋ የተቃኙ የራሳቸውን እውነቶች እንዲጽፉ ቦታ ይፈጥራል እንጂ።

ገጣሚያኑ እንዲሁ ሰላምን ለመስበክ ወይም ለማወደስ ሳይሆን አስፈላጊነቱን እውቅና እንዲሰጡ፣ ክብደቱን ፣ መጥፋቱንና በቅርበት በሕይወታችን ውስጥ ያለና ተንከባክበን ልንይዘው የሚገባ ተሰባሪ ውድ ነገር መሆኑን እንዲመሰክሩ ይጋበዛሉ።

ለመሳተፍ የሚያስችሉ ሁነቶች

መላው የኢትዮጵያና የኤርትራ ተወላጆች እንዲሁም ከሀገር ውጭ የሚኖሩ ገጣሚያን ሁሉ መሳተፍ ይችላሉ፤ የሙያ ደረጃ ገደብ የለውም።

የማቅረቢያ መመሪያዎች

የሚቀርበው ስራ፡- እስከ 3 (ሶስት) ያልታተሙ ግጥሞች (በአጠቃላይ ከ5 ገፆች ያልበለጠ)።

የማመልከቻ መንገድ፡–  በዚ ድረ-ገጽ ላይ ‘’Google ፎርም’’ በመሙላት ብቻ ያመልክቱ።

የጽሁፍ ቅርጽ፦ ሁሉም ግጥሞች በአንድ የተሰነዱ መሆን አለባቸው (በ .doc, .docx, .rtf, .txt ወይም PDF)። የፊደል ይዘት፦ Times New Roman/Arial/Calibri፣ 12 ቁጥር ፣ ነጠላ ወይም 1.5 ክፍተት፣ መደበኛ ህዳጎች ያሉት መሆን አለበት።

ቋንቋ፡– በኤርትራና በኢትዮጵያ የሚነገሩ ወይም የሚጻፉ ማንኛውም አይነት ቋንቋዎች።

የማመልከቻ መጨረሻ ቀን፡- ሚያዚያ 18. 2018 ዓ.ም  

ትርጉም

ስራው ከተመረጠ በኋላ በባለሙያ ቋንቋዊ፣ ባህላዊና ግጥማዊ ታማኝነትን በሚጠብቅ መንገድ በተቻለ መጠንም ከገጣሚው ጋር በመመካከር ትርጉሙ ይዘጋጃል።የግጥም ስብስቡ የመጀመሪያውን ቋንቋና የእንግሊዝኛ ትርጉሙን ጎን ለጎን የያዘ ይሆናል።

አስፈላጊ ማስታወሻዎች

ገጣሚያኑ ስራዎቻቸውን በአንድ ጊዜ ፥በአንድ ፋይል፥ አንዴ ብቻ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ ፤ መልስ እስኪደርሳቸውም ድረስ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። በአንዴ ብዙ ጊዜ ማመልከት ሁሉም ሳይታዩ እንዲያልፉ ያደርጋል። 

ያልታተመ ስራ ብቻ፡- ግጥሞች በማንኛውም ምክንያት በህትመት ወይንም በድረ-ገጽ ላይ ያልታተሙ መሆን ይኖርባቸዋል። በማህበራዊ ሚዲያ፣ በግል ድረ-ገጾች ወይም በብሎጎች የተጋሩ ስራዎች እንደታተሙ ይቆጠራሉ።በተመሳሳይ ጊዜ ሌሎች ቦታዎች መወዳደር ይቻላል ፤ ስራቸውው በሌላ ቦታ ተቀባይነት ካገኘ ግን ገጣሚያኑ ወዲያውኑ በ peneritrea@gmail.com ኢሜል ለአርትኦት ቡድኑ ማሳወቅ ይገባቸዋል።በኢሜይል የተላኩ ማመልከቻዎች ተቀባይነት የላቸውም።

የግጥም ስብስቡ የሚፈልገው፦

ገጣሚያኑ ስራቸውን በራሳቸው መንገድ የማቅረብ ነፃነት እንዳላቸው እንዲያውቁ፤ እነዚህ ነጥቦች ማመሳከሪያ እንጂ ግዴታዎች አለመሆናቸውን ነው።

የአርትኦት አተገባበር 

ይህ የግጥም ስብስብ የስነ-ጽሁፍ ነፃነትንና ሀሳብን በነጻነት መግለጽን በአጽንኦት ያከብራል ይጠብቃልም። ግጥሞች የሚመረጡት በሥራቸው ውስጥ በተገለጠው ክህሎት፣ በፈጠራዊ ወጥነት፥ በፈጠራ ታማኝነት እንጂ ከማንኛውም ፖለቲካዊ አቋም ወይም አጀንዳ ጋር ባላቸው ወገንተኘነት አይደለም ። የአርታዒ ቡድኑ ስነ-ጽሁፍን እንደ ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ መጠቀምን በግልጽ ይከልክላል። ስነ-ግጥም የትኩረት፣ የጥያቄና የምናብ ነፃነት መኖሪያ ፤ እንዲሁም ውስብስብነት በራሱ እንዲቆም የሚፈቀድበት፣ ገጣሚያኑም ያለ መመሪያና ያለ ግዴታ ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ስፍራ ነው። በዚህ ስብስብ መካተት ከገጣሚያኑ አመለካከት ጋር መስማማትን አያመለክትም፤ መታተምም የማንኛውንም አመለካከት መደገፍ ወይም ማጽደቅን አይጠቁምም። ይህ ከምንምና ከማንም የሀሳብ ጫና የፀዳ የጋራ የስነ-ጽሁፍ ስፍራ ነው።

መብቶች እና ክፍያ

የቅጂ መብት፦ ገጣሚያን በስራቸው ላይ ሙሉ የቅጂ መብት ይዞታ አላቸው፤ ይህ መብት ምንግዜም የፀና ይሆናል።

የህትመት መብት፦ ገጣሚያኑ የተመረጡላቸው ግጥሞች በህትመትና በዲጂታል መልክ እንዲታተሙ፤ እንዲሁም ስራውን ለማሰተዋወቅ በሚረዱ የተለያዩ መንገዶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቃድ ይሰጣሉ።

ክፍያ፦ ስራቸው የተመረጠ ገጣሚያን $200 (ሁለት መቶ ዶላር) ክፍያ ይቀበላሉ።

የማመልከቻ ጊዜ እና ምርጫ

የመላኪያ መጨረሻ ቀን፡ሚያዚያ 18. 2018 ዓ.ም

የምርጫው አካሄድ በስራ ጥራትና ብቃት ብቻ የተመሰረተ ይሆናል ። የተመረጡ ስራዎች ማሳወቂያ ከመጨረሻው የማመልከቻ ቀን በኋላ ባሉት 8 (ስምንት) ሳምንታት ውስጥ ይሆናል።

የተመረጡ ገጣሚያን ብቻ ከአዘጋጆቹ መልዕከት ይቀበላሉ።

በሚቀርቡ ስራዎች ብዛትና የስራ መደራረብ ምክንያት ለቀረቡ ስራዎች በየግል አስተያየት አይሰጥም። 

ጥያቄዎች ካሏችሁ፡-peneritrea@gmail.com ይጻፉ።